ክቡር አምባሳደር ፍቃዱ በየነ የክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የጠቅላይ ሚኒሰትር በያዝነው ሳምንት በበርሊን በተካሄደው የCompact with Africa Conference ወቅት ከጀርመን ቻንስለር Olaf Scholz ጋር ውጤታማ ውይይት ያደረጉበት መሆኑን አብራርተዋል፡፡ አያይዘውም በዚሁ ሳምንት ከጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር የፖለቲካ ኮንስልቴሽን እንዲሁም የኢትዮ-ጀርመን የንግድና ኢንቨስትመንት መካሄዱን ገልጸው፣ሁለቱም ስኬታማ እንደነበር በዝርዝር አስረድተዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም አምባሳደር ፍቃዱ ወቅታዊ የአገራችንን ሁኔታ የሽግግር ፍትህና የብሔራዊ ምክክር ሂደት ያለበትን ደረጃ ገልጸውላቸዋል፡፡

Mr. Knill የሚመራ የልአካን ቡድን አስር አባላት ያሉት ከኮቪድ-19 በኃላ  ለመጀመሪያ ግዜ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ወደ ኢትዮጵያ በመሄድ ለስተራክቸራል ትራንስፎርሜሽንና ለተለያዩ ፕሮጀክቶች የቴክኒክና ፋይናንስ ድጋፍ ለመስጠት ለድርደር ወደ ኢትዮጵያ እንደሚሄድ ገልጸዋል። አያይዘውም ጀርመን ቀደም ሲል ለኢትዮጵያ ድጋፍና ትብብር የምታደርግባቸውን መስኮች አሁንም ለማገዝ ትልቅ ፍላጎት አንዳለ ጠቅሰዋል፡፡ በዚሁ ስብሰባ ላይ አብረዋቸው የተገኙት Mr. Marcus Von Essen, Head of Division East Africa በበኩላቸው በተመሳሳይ ቀደም ሲል በጀርመን በኩል ድጋፍ ሲደረጉ የነበሩትንና የተለያዩ ሴክተሮችንም አስመልክቶ በዚሁ ውይይታቸው አንደሚካተቱ አክለው ገልጸዋል፡፡

በመጨረሻም ክቡር አምባሳደር በኢትዮጵያ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ሴክተሮች አብራርተው እሰከዛሬ በጀርመን መንግሰት ስለተደረገውም ድጋፍ አመስግነዋል፡፡

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook