(ኅዳር 12 ቀን 2016 ዓ.ም) የኢትዮጵያ – የጀርመን ኢንቨስትመንት እና ንግድ ፎረም/Ethiopia -Germany Trade and Investment Forum ኅዳር 12 ቀን 2016 በርሊን ተካሄዷል ።
ክቡር ዶክተር ኢዮብ ተካልኝ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ ለፎረሙ ተሳታፊዎች ባደረጉት ገለጻ፤ የኢትዮጵያ – የጀርመን ኢንቨስትመንት እና ንግድ ፎረም/Ethiopia -Germany Trade and Investment Forum የኢትዮጵያን ተሞክሮ በተለይም የኢትዮጵያ ትኩረት በተሰጠቻቸው የኢንቨስትመንት መስኮች የግሉ ሴክተር ኢንቨስት በማድረግ ተጠቃሚ ሊሆንባቸው የሚችሉ አማራጮችን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በፎረሙ ላይ የጀርመን ተቋማት የሥራ ሓላፊዎች Ms. Sabine Dall’Omo Chairperson,
Afrika-Verein der deutschen Wirtschaft (AV) እና Ms. Ursula BORAK Deputy Director General for the Economic Affairs and Climate Action (BMWK) of the Federal Republic of Germany በሁለቱ ሀገራት መካከል ስላለው የኢኮኖሚ ትስስር በመግለጽ የጀርመን ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል ።
በጀርመን የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደርና ልዩ መልእክተኛ ክቡር አምባሳደር ፍቃዱ በየነ በኢትዮጵያ ሰፊ የኢንቨስትመንት ዕድል፣ ምቹ የአየር ሁኔታ፣ የመንግስት ቁርጠኝነትንና ድጋፍ፣ የሚሰጡ የኢንቨስትመንት ማበረታቻዎችን፣ ሰፊ ገበያ እና የሠለጠነ ወጣት የሰው ሀብት መኖሩን ወዘተ. ለተሳታፊ ባለሀብቶች እና ካምፓኒዎች አስረድተዋል፡፡
በWAFA Marketing Promotion የተዘጋጀ ዶክመንተሪ በኢትዮጵያ እና በጀርመን ያለውን የንግድ እና የኢንቨስትመንት የሁለትዮሽ ግንኙነት ለተሳታፊዎች ለእይታ ቀርቧል።
በቢዝነስ ፎረሙ ላይ ጠቅላላ ገለጻ/Presentation/ እና የተለያዩ የፓናል ውይይቶች የተካሄዱ ሲሆን በወይዘሮ ዑባህ መሐመድ በጀርመን የኢትዮጵያ ኤምባሲ የኢኮኖሚ እና ቢዝነስ ዲፕሎማሲ ዘርፍ ሓላፊ በኢትዮጵያ ትኩረት ስለተሰጣቸው የኢንቨስትመንት ዋና ዋናዎቹ ዘርፎች ገለጻ የቀረበ ሲሆን በ Ms. Mildred Nadah Pita Head of Public Affairs, Science & Sustainability Bayer AG, Germany ካምፓኒያቸዉ በኢትዮጵያ ስላለው ስኬታማ ተሞክሮ ለተሣታፊዎች አቅርበዋል ።
ከጠቅላላ ገለጻና ውይይቶች በተጨማሪም B2B and Matchmaking ውይይቶችም ተካሄዷል ፡፡
   

Disclaimer: The official text of the Embassy Website is the English language version. Any discrepancies or differences created in translations are not binding and have no legal effect for compliance or enforcement purposes.

X
Twitter
Facebook